የተገኘው
መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ጊዜ በመላው የኦሮምያ ክልል እየቀጠለ በሚገኝ ተቃዉሞ እና በየቀኑ በሚያጋጥም ግጭት ተከትሎ በገዢው
የኢህአዴግ ስርአት በሰላማዊ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ የሚገኝ የመግደል እና የማሰር እርምጃ ተማርረው ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ ለገቡ
ዜጎች የኬንያ መንግስት ተቀብሎ በማስገደድ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት እያስረከባቸው እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ አመልከተ።
በዚህ
መሰረት ደግሞ በላፈው ታሕሳስ
22ና 23 ቀን 2008 ዓ.ም 25 ኢትዮጵያዉያን በሞያሌ
አካባቢ ለስርአቱ የተሰጡ ዜጎች አሉ በማለት የኦሮሞ ማሕበረሰብ ተወላጆች ከናይሮቢ የገለፁ ሲሆኑ ከተጠቀሱ ሰዎች በተጨማሪም
41 የሚሆኑ ዜጎች በኬንያ ፖሊስ ቁጥጥር ዉስጥ ገብተው ስለሚገኙ
የኬንያ መንግስት ወደ ኢትዮጵያ መንግስት አስተላልፎ እንዳይሰጣቸው በሚል ስጋት አሳሳቢ ሆኖ እንደሚገኝ የኦሮም ማሕብረሰብ ጨምረው
ገልፀዋል።