አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተጣባቂ / ሁማን ራይትስ ዎች/ በታሕሳስ 29 ቀን 2008 ዓ/ም ባወጣው መግለጫ እንደገለፀው፣ በአዲስ አበባ ከተማና
በዙርያዋ የሚገኙ ልዩ የኦሮምያ ዞን ከተሞች በመሰረተ ልማት ለማስተሳሰር በሚል የወጣው ሰንካላ አዋጅ ተከትሎ በተነሳው ተከታታይ ህዝባዊ
ተቃውሞ በታጠቁ የገዥው ስርአት ካደሪዎች
የተገደሉ ንፁሃን ዜጎች ከ40 በላይ መድረሳቸው አሳውቀዋል።
አለም አቀፍ ድርጅቱ ጨምሮ እንዳስረዳው፣ የተነሳው ህዝባዊ
ተቃውሞ በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎችና በሁለትኛ ደርጃ ትምህርት ቤቶች
ብቻ ሳይሆን በሩቅ የሀገሪቱ ገጠሮች የሚገኙ ገበሬዎችም እንደተሳተፉበትና
የተገደሉት ዜጎች ቁጥርም ከተቀመጠው አሃዝ ሊበልጥ እንደሚችልና፣ 140
የተባለው የፀጥታ ሃይሎች በትክክል የተገደሉት በስእል የተደገፈና እውነተኛ ማሰረጃ መሰረት
ያደረገ መሆኑ መግለጫው ጨምሮ አስረድቷል።