Tuesday, January 5, 2016

በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ጋንታ አፈሹም ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች የስፍትኔት ስራ በአድልዎ እየፈፀሙ መሆናቸው ከአከባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ።



   በስራቃዊ ዞን ጋንታ አፈሹም ወረዳ ሃገረሰላም ቀበሌ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ድሃው ሕብረተሰብ ሰርቶ ህይወቱን ለመምራት በሚል በዉጭ አገር ደጋፊ ተቓማት የሚሸፈን ሰፍትኔት ቢጀምርም በአተገባበር ስራ ግን በአድልዎ እና ጉቦ እንዲሰራ እየተደረገ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው፣ በአንፃሩ የሚጦራቸው ሰው ያጡና የሰማእታት ቤተሰብ እንዲሁም ታጋዮች ነበር በሰፍትኔት እንዲገቡ ጠይቀው የሚያያቸው የመንግስት አካል እንደሌለ ታዉቀዋል።

   መረጃው አስከትሎ ለአቅመ አዳም የደረሱ በርካታ ወጣቶች በስራ እጦት ምክንያት ለእርሻ የሚሆን መሬት አጥተው በከባድ ችግር ደርሰው እያሉ የቀበሌው አስተዳዳሪዎች ግን የሞቱት እና ያሉት የእርሻ መሬት ደርበው በመያዝ ለግላቸው እየተጠቀሙበት እንደሚገኙ የሚታወቅ ሆኖ፣ ነዋሮዎቹ የመልካም አስተዳደር ዋነኛ ችግር  እየሆኑ ያሉትን አስተዳዳሪዎች በሕግ ቀርበው ስለማይጠቁ ነው በማለት ተቃዉሞቸዉን እንዳሰሙ ታዉቀዋል።