Tuesday, January 5, 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በጠቅላላው 18 ሚሊዮን መሆኑ ዩ.ኤስ.አይ.ዲ የተባለ አለማቀፍ ተቋም አሳታወቀ።



በተገኘው መረጃ መሰረት፣ በአለም አቀፍ ተቋም ዩ.ኤስ.አይ.ዲ የውጪ ልማት ሃላፊ የሆነ ጀረሚ ካናንዳይክ ሲሆኑ በፈረጅ አቆጣጠር በአዲስ አመት መግቢያ 2016 ምክንያት በማድረግ  በሚዲያዎች ቀርቦው  ባደረጉት  ቃለ መጠይቅ በኢትዮጵያ ወስጥ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ወገኖች በጠቅላላው ወደ 18 ሚሊዮን ከፍ እንዳለ አስረድቷዋል።

    የድርጅቱ  ባለስልጣን  ባደረጉት ቃለ መጠይቅ በሰጡት የማብራሪያ ሃሳባቸው የኢትዮጵያ መንግስት እርዳታ ያስፈልገኛል ብሎ የገለፃቸው  10.2 ሚሊዮን ወገኖች በመርህ ግብር ወስጥ፣ ከአሁን  በፊት በሰፍቴኔት ከታቀፉ 8 ሚሊዮን ወገኖች ተጨማሪ ነው በማለት በዚህ መሰረት አስቸኳይ የምግብ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ኢትዮጵያዊያን 18 ሚሊዮን ነው ሲሉ አብራርተዋል፣