Friday, January 8, 2016

የህዝብ ጥያቂ በማፈን ስደትን በአዋጅ አይገታም!



       ስደት ለአንድ አገር ህልዉናና ድህንነት እያልክ  በፈለክበት ግዜ በምታወጣው አዋጆችና እና መምርያዎች የሚታገት ሳይሆን ገና በጥዋቱ ሰላም ልማት ፍትሕ መልካም አስተዳደር እና ዴሞክራሲን በማንገስ ዜጎች የአገራቸው ሃብት በእኩልነት በሚጠቀሙበት አሰራር በሚያረጋግጥ መልኩ በመዘርጋት። በአገራቸው እና በመንደራቸው ላባቸው አፍስሰው  የሚጠቀሙበት  ሰፊ የስራ እድል አግኝተው ሲኖሩ ብቻ ነው፣
     ስልጣን የተቆጣጠረውን ስርአት ህዝባዊ ስርአት ነው የሚባለው ሁሉም የአገሪቱ ዜጎች የሚሳተፉበት እና የሚያምኑለት ትክክለኛ የልማት ፖሊሲ በመከተል ከጊዜ ወደ ጊዜ በዜጎች ማሕበራዊ ህይወት ላይ ለዉጥ እየፈጠረ ህልዉናቸው ተጠብቆላቸው ሲኖሩ ሲያድርግ ነው፣
    በተመሳሳይ ውስጣዊ ሰላም እና መረጋጋት አንግሶ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ በተሻለ እድገት አረጋግጦ ብሎም አሳታፊ የሆነ ፖለቲካዊ አስተዳደር። የሰበአዊ እና ዴሞክራስያዊ መብቶች ማክበር ተጠያቂነት ያለው ህዝባዊ ፖለቲካዊ ስልጣንና። የነጠረ ስትራተጂ ህዝብ እንዲሟላለት ስለ ሚፈልግ ለዚህ ህዝብ የሚፈልገዉን ጥያቄ የሚመልስ ፖለቲካዊ ባህሪ እና ግብራዊ የሆነ ድርጅታዊ አሰራር መኖር አለበት፣
      የተጠቀሱ ጥያቄዊች እና ፍላጎቶች ባልተረጋገጡበት ግዜ ግን ዜጎች አገራቸው ለቀው ሌላ የባእድ አገር ማየታቸው ባህርያዊ ነው፣ በመሆኑ በአሁኑ ግዜ ሰዎች በህጋዊ መንገድ ይሁን ከህግ ዉጭ አገራቸው ትተው በባህር እና ምድረ በዳ በመቛረጥ በባሰ መልኩ የተሻለ ንሮ ወደ ሚገኝባቸው የአረብ አገሮች በስደት ለመግባት በሚመኩሩበት ጊዜ። በየቀኑ የዜጎቻችን ህይወት በረሃብ እና በተለያዩ ችግሮች እንዲሁም በተለያየ በረሃዎች ህይወታቸው ሲያልፍ የተቀሩት ደግሞ በባህር የአሳ እራት እየሆኑ ነው ብቻ ሳይሆን። የሰዎች ዉስጣዊ አካል እንደ እንስሳት እየታረደ የዶላር ምንጭ ገቢ በማድረግ በዜጎች ላይ ሰይጣናዊ የሆነ ዓላማ አንግበው ጀምላዊ እልቂት በመፈፀም ስራ በተሰማሩ ደላላዎችና ሽብርተኞች አለማችን እየተቸገረች እንደምትገኝ የሚያጠያይቅ ጉዳይ አይደለም፣
     በየጊዜው ከተለያዩ አገሮች እየተሰደዱ ወደ አዉሮፓ አገሮች የሚገቡ ወገኖችም። በአዉሮፓ ህብረት ለችግሩ ለማገት ያልተደረገ ስምምነት የለም ብቻ ሳይሆን።  በመሬት ተጉዘው የሚገቡ ሰራተኞች ለማገትም። ለመግብያው በአጥር በመዝጋት ለማቛረጥ ቢመኮርም እየባሰ እንጂ እየቀነሰ ሲሄድ አልታየም፣
    በዚህ መሰረት አገራችን ኢትዮጵያ የዚህ ሰለባ አካል በመሆንዋ የተነሳ። በስልጣን ላይ በሚገኘው ኢ-ዴሞክራስያዊ ስርአት በፈጠረው ብልሹ አስተዳደር ምክንያት ዜጎቻችን በአገራቸው እንዳይኖሩ መሰረታዊ የህይወት ዋስትና በማጣታቸው። ሊሟላላቸው የጠየቁት የመብት ጥያቄ በኃይል ታፍነው። ፍትሕ በማጣታቸው ምክንያት ወደ ስደት ሲያመሩ ህይወታቸው ሲያልፍ ቆይተዋል አሁንም እየቀጠለ ይገኛል፣
    የኢህአዴግ መሪዎች ዜጎቻችን ከአገራቸው እና ቤተሰዎቻቸው ተነጥለው ወደ ስደት እንዲያመሩ እያደረጋቸው ያለ መንስኤ ጥናት በማድረግ ዘላቂ መፍጥሄ ከማስቀመጥ ይልቅ። እንደተለመደው በይስሙላ የፓርላማ ስብሰባቸው በላፈው ሳምንት ለዜጎች ድህንነት በሚል ሰንካላ ምክንያት አዋጅ አዉጥተናል በማለት ዝርዝር ነጥቦች ሲገልፁ ታይተዋል፣
   በአገራችን ይህ አዋጅ ቢታወጅም በካድሬዎች እና በስርአቱ የፀጥታ ሃይሎች በየቀኑ ፀጉር ለወጥ በሚል ጥርጣሬ  ስም እየታሰረ እና እየተፈታ የሚዉለው ህዝብ በከፋ መልኩ ነፃነትና መብት አጥቶ እየታፈነ እንጂ ሌላ ለድህንነቱ የሚጠብቅ የመጣ ለዉጥ የለም፣
    ምክንያቱ ህዝባችን መሰረታዊ ጥያቄዎቹን መፍጥሔ አጥቶ ለተዳራራቢ ችግሮች ተጋልጠዋል ብቻ ሳይሆን ዴሞክራስያዊ እና ሰብአዊ መብቶቹ ተፋኖ እና ተረግጦ ባለበት በአሁኑ ጊዜ። ስደት በአዋጅ ሊታገት በፍፅም ስለማይቻል፣