የመረጃ ምንጮቻችን እንደሚያመልክቱት፣
ይህ እየተካሂደ ያለው በገዢው ስርአት ላይ ያተኮረ ተቃውሞ፣ የአዲስ አበባ ከተማና ዙሪያዋ በፊንፊኔ ማስተር ፕላን የተሳሰረ ሲሆን፣
ይህ እየተካሂደ ያለው ተቃውሞ የኢህአዴግ ገዢው ቡድን እደሜ ሰልጣኑን ለማራዘም በሚል በረካታ የፖለቲካ ድርጅቶች ማጥቃቱ ይቁም፤ ገዢው የኢህዴአግ ሰረአት የተቃውመውን ሰው አሸባሪ እያለ ማሰር ያቋርጥ፤
ህዝብ የመቃውም የመፃፍ መብት ሊኖረው ይገባል፤ በዚህ ሰርአት የተገደሉ ዜጎች ለቤተሰቦቻቸው ካሳ መከፈል አለበት የሚል መፈክር ያሰሙ ያሉ መሆኑ ተገለፀ።
መረጃው አሰከትሎ እንዳሰረዳው፣
በእዚህ ወቅት የተቃውሞ ሰልፍ እየተካሄደባቸው የሚገኙ የሃገራችን አካባቢዎች ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ በተለይ ደግሞ በምሰራቅና ምእራብ
ሃረርጌ፣ በሂርና ከተማ ጭሮ ወረዳ አዳኩሉ መኢሶ የሚገኙ ከተማዎችና የገጠር ቦታዎች፣ በታህሳስ 29 /2008ዓ/ም ከቀኑ 6-9 ሰአት በተካሂደ ከባድ ሰላማዊ ሰልፍ፣ ኢህአዴግ በፖለቲካ ሊሰራና ሊመራ
ይገባዋል እንጂ በሃይል ህዝብንም ይሁን ተቃውሞን መጨፈለቅ አይገባም፣ እያሉ ተቃዉማቸዉን በሚያሰሙበት ግዜ፣ በጭሮ ከተማ ብቻ 20
ሰልፈኞች በገዢው የኢህአዴግ ሰርአት የፀጥታ ሃይሎች በከባድ እንደቆሰሉ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ ከህዳር 4/ 2008 ዓ/ም ጀምሮ እየተካሂደ ያለው ተቃውሞ ህዝቡ በሃይል ለማቆም እየጣረ ያለው ገዢው ሰርአት፣
እስከአሁን ድረስ ከ140 በላይ ንፁሃን ዜጎች እንደገደለ በአለም አቀፍ ተቋም ተረጋግጦ እያለ፣ ስርአቱ ግን 5 ሰዎች ብቻ እንደገደለ
ነው የሚገልፀው።
No comments:
Post a Comment