በአገራችን ኢትዮጵያ ዜጎች በስራ እጥነት፤
በትምህርትና በሌሎችም ምክንያት ከአገራቸው ወደ ሌላ አገር ለስደት
እንዲሄዱ መገደዳቸውና በተለይ ደግሞ የተማሩ ዜጎች በተማሩት የትምህረት
አይነት መሰረት የስራ እድል ስለማያገኙ በዚህ ሳብያም ለፖለቲካና ለማህበራዊ ችግሮች ስለተጋለጡ ከአገራቸው
ወጥተው ወደ ስደት ሊያመሩ ምክንያት መሆኑን ታውቀዋል።
በ2007 ዓ/ም በአለም ደረጃ በተደርገው ጥናት መሰረት የሰደተኞች ቁጥር
ወደ 250 ሚልዮን መድረሱንና ከእነዚህም በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ጥናቱ ካስቀመጠ በኃላ በዚህ ስደትም በርከት ያሉ ኢትዮጵያውያን ለከባድ አደጋዎች መውደቃችወና በተለይ ደግሞ
በሊብያ በአስከፊ ሁኔታ ለተገደሉት 30 ዜጎቻችን ምሳሌ መሆናቸውን
መግለጫው አስረድተዋል።
መግለጫው ጨምሮ
በምሰራቅ አፍሪካ ከሚገኙት በተለይ ደግሞ በስደት ምክንያት
በመደረስ ላይ ያለው የኢትዮጵያ የወጣቶች ፍልሰት ለመቀነስ በስልጣን
ላይ ያለው መንግስት ጥረት ባለማድረጉ ሁኔታው ከጊዜ ወደ ጊዜ ተባብሶ መቀጠሉ የሚያሳስብ ጉዳይ እየሆነ መምጣቱ ያገኘነው መረጃ አስስረድተዋል።
No comments:
Post a Comment