Thursday, February 18, 2016

በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲዳረስ ተደርገዋል በማለት የወጣውን ሪፖርት ተቀባይነት የሌለው ነው ሲሉ ብዙ ወገኖች በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።



የገዢው ኢህአዴግ ስርአት ትምህርት ሚኒስተር ባወጣው ሪፖርት መሰረት፣ እድሜያቸው ከ7 እስከ 8 እድሜ የደረሱ ህፃናት፣ 95 ከመቶ የመጀመሪያ የትምህርት እድል ሊያገኙ ችሏል፣ በተጨማሪም ወደ ትምህርት ቤት ለመግባት ትክክለኛውን የእድሜ ክልል የሚገኙ 7 አመት የሞላቸው 86 ከመቶ ወደ ትምህርት የመግባት እድል ሊያገኙ ችሏል፣ ተብሎ በትምህርት ሚኒስተር የወጣውን ሪፖርት፣ ከሃቅ የራቀ ሪፖርት ነው ሲሉ ብዙ ወገኖች እየተቃወሙት እንዳሉ ታወቀ።
  ሪፖርቱን ተከትሎ በተለያዩ ሙሁራን በኢትዮጵያ  በተለያዩ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች ቢሰሩም እንኳ፣ በብዙ የአገራችን ገጠሮች ትምህርት ቤቶች እንደሌላቸውና በሌሎች ደግሞ ተማሪዎች በዳስ እየተማሩ እንዳሉ ከገለፀ በኃላ፣ ተስርተዋል እየተባሉ ያሉትን ትምህርት ቤቶችም ቢሆን፣ ስርአቱ ለትምህርት ትኩረት ሰለማይሰጠው ብዙ ችግሮች እንዳሉዋቸውና የትምህርት ጉዳይ ሲነሳም አብዛኛው የህብረተሰቡ ክፍል በትምህርት ቤት ውስጥ ሊሟሉ የሚገባቸው መሰረታዊ ግብአቶች ሊሟሉ ባለመቻላቸው። ተማሪዎች ትምህርታቸውን በአግባቡ ሰለማይከታተሉ ወላጆች በትምህርቱ ላይ ተስፋ እንደሌላቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment