Sunday, November 26, 2017

በደቡባዊ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ የሚገኙ ነዋሪዎች መንግስት ለልማት ብሎ መሬታቸው በመዉሰድ ከቦታቸው እንዳፈናቀላቸውና ተገቢ ካሳ እንዳልተሰጣቸው አስታወቁ።



በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን መካነ ሰላም ከተማ የሚኖሩ ዜጎች መሬታቸው ለልማት በሚል ምክንያት የተወረሱ ዜጎች ተፈናቅለው እስከአሁን ድረስ ካሳ ባለማግኘታቸው በችግር ላይ ወድቀው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
በመቅደላ ዩንቨርስቲ ግንባታ ምክንያት ከአከባብያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች እንዳሉና እስካሁን ደግሞ የተሰጣቸው ካሳ በቂ እንዳልሆነ እየተገለፀ ሲሆን፥በተጨማሪም አሁን ሰፍሮውበት የሚገኙ አከባቢ ቢሆንም በቂ መሰረተ ልማት እንዳልተሟላላቸው በተለይ ድግሞ መብራትና ንፁህ የመጠጥ ዋሃ ባለሞኖሩ በእለታዊ ኑሯቸው ተቸግረው እንዳሉ አማርሯል።
ይህ እንዲህ እንዳለ ወ/ሮ ወደር የለሽ የተባሉት የከተማዋ ነዋሪ በመካነ ሰላም ከተማ ለ58 ዓመታት ገደማ እንደኖሩና መሬት ይሰጠኝ በለው ለአመታት ጠይቀው መልስ የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው በምሬት ገልጸዋል።
በአከባቢው የሚገኙ የኢህአዴግ ካድሬዎች ሴትየዋ እያቀረቡት የቆዩ ተደጋጋሚ ጥያቄ መልስ ሳይሰጡ የሰፈራችሁብት ቦታ የቀበሌ ነው የሚል የሚያሳዝን መልስ እንደሰጧቸውና ተወልጀ ያደኩበት መሬት እንዳይከለከል ሰግቻለው ሲሉ ገልጸዋል።




No comments:

Post a Comment