Sunday, November 26, 2017

ባለፈው አመት ከተካሄደ በጥልቅ የመታደስ መድረክ በኃላ በአከባብያችን መልካም አስተዳደር መንገስ አልቻለም ሲሉ በአክሱም ከተማና አከባቢዋ የሚገኙ ወገኖች ገለፁ።



በአከባቢው በመሬት፣ በካሳና በልማት ተጠቃምነት ትልቅ ክፍተት መኖሩ እንዲሁም የአከባቢው ህዝብ ለሚያቅርብላቸው ጥያቄዎች መልስ እንደማይሰጣቸው አስረድቷል።
መሬት በከተማ ይሰጠን ብለው ለጠየቁ ዜጎች እናንተ ድሃዎች ናቹ አይገባቹሁም የሚል መልስ ተደጋጋሚ እንደሚሰጣቸው የገለፁት ነዋሪዎቹ በተጨማሪ ደግሞ በከተማዋ የሚገኙ የሕወሓት ካድሬዎች በግቦና ጥቅማ ጥቅም ያደሉት በርከት ያለ ካሬ ሜትር ያለ ሆኖ እስከአሁን ድረስ ግንባታቸው ጀምረው በጥቅም እንዳልዋሉ ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም በከታማዋ ማለቅያ የሌላቸው የህዝብ አቤቱታዎች በየቀኑ እንደሚታዩ የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ተገቢ መፍትሔ ከመስጠት ይልቅ ስራ አለን በስብሰባ ላይ ነው ያለነው የሚል ሰንካላ ምክንያት እንደሚያዘወትሩ ገለፁ።
 ይህ እንዳለ ሆኖ የአክሱም ከተማ መዘጋጃቤት የመሬት ወረራ የመከልከል ስልጣን እያለው ህዝብ የሰጠው ሃላፍነት ለጎን በመተው ለራሱ የህዝብ መሬት በመውረር ተሰማርቶ እንዳለ ተገለፀ።
ከነዚህ በመዘጋጃቤቱ የተወረሩ የህዝብ መሬት ደግሞ የወጣቶች ማሕበርና የመምህራን ማህበር መሆናቸው ነዋሪዎቹ በምሳሌ አስደግፈው አረጋግጠዋል።
በደርግ ጌዜ እንዃ መሬታቸው ያልተወሰደባቸው ዜጎች በወያኔ ስልጣን ዘመን እንደተወሰዱና መሬታቸው እንዲመለስላቸው ስድስት አመታት ሙሉ  ጠይቅው መፍትሔ እንዳላገኙ አስረድቷል።


No comments:

Post a Comment