Wednesday, December 26, 2012

ከ 1990 ዓ/ም ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት ሲያገለግሉ የቆዩ ወታደሮች የስንብት መልቀቅያ እንዲሰጣቸው ከያሉበት የጦር ክፍል መጠየቅ ጀመሩ ።


በመከላከያ ሰራዊት መተዳደሪያ ህግና ደምብ መሰረት አንድ ወታደር በሚመለመልብት ግዜ ለ 7 ዓመታት በሞያው ለማገልገል ውል ይፈርማል ፥ እንደየ ሁኔታው እየታየም በየ 7 ዓመቱ ውሉን በማደስ በውትድርና ሞያ መቀጠል አልያም ላለመቀጠል መብቱ አለው ። ነገር ግን አምባገነኑ የኢህአደግ ስርዓት እስካሁን ድረስ አሰራሩን ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻሉ ከሰራዊቱ መሰናበት የፈለጉ የሰራዊት አባላት መብታችን ይከበርልን በማለት መጠየቅ ጀምረዋል ።
በደረሰን ዘገባ መሰረት ስንብት ለሚጠይቁ ወታደሮች ከሰራዊቱ አዛዦች የሚሰጠው መልስ አገሪቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ስለሆነች ስንብት አይፈቀድም የሚል መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
በአሁኑ ግዜ በሰራዊቱ ውስጥ ስንብት የሚጠይቁ ወታደሮችን እንደ ከሃዲ በመቁጠርና በማስፈራት ማስጠንቀቅያ እንደሚሰጣቸው የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል ።