በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የ2ኛ ደረጃ
ት/ቤት አስተማሪዎች በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ባለፈው ዓመት የደመወዝ ጭማሪ ማድረጉን በመገናኛ ብዙሃን ቢገልፅም እስካሁን
ግን ምንም አይነት ጭማሪ እንዳልተደረገላቸው ከአካባቢው የተገኘ መረጃ አስታወቀ።
መረጃው በማስከተል
አስተማሪዎቹ ለምን ደመወዛችንን አልተሰጠንም ብለው ለክልሉ ትምህርት ቢሮ ቢጠይቁም የተደረገውን ጭማሪ ለመጀመርያ ዲግሪ ሳይሆን
ለሱፐርቫይዘሮች ብቻ ነው ተብሎ መልስ በመሰጠታቸው ስርአቱ ቃሉንና ተግባሩን የማያከብር ከዳተኛ ነው በማለት ብሶታቸውን በማቅረብ
ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።
ባለፈው ዓመት የደመወዝ ጭማሪ መደረጉ ቢገለፅም ነገር ግን በሁሉም የሃገሪቱ
ክልሎች ተግባራዊ ስላልሆነ አስተማሪዎች የሚገኙባቸው በርካታ ሰራተኞች ያጋጠማቸውን የኑሮ ውድነት አስመልክተው ጥያቄዎችን ቢያቀርቡም
ችግራቸውን የሚፈታላቸው አካል እንዳላገኙ ምንጮቻችን አክለው አስረድተዋል።