በአዊ ዞን በጃዊ ወረዳ በጣና በለስ አከባቢ ሰፍረው የነበሩ ገበሬዎች ቀደም ሲል በኦሮምያ ክልል ይኖሩ
የነበሩ ሲሆን የኢህአደግ ስርዓት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት ከክልሉ ተፈናቅለው በጣና በለስ አከባቢ የሰፈሩ መሆናቸውን
ለማወቅ ተችለዋል ።
መንግስት ሃይል በመጠቀም በአከባቢው ይኖሩ የነበሩ ገበሬዎችን የግል ንብረታቸውን ግምት በአግባቡ ሳያገኙ ምንም ዓይነት ቅድመ ዝግጅት ሳይደረግ ከቀያቸው በማፈናቀል ሰንደቃ በተባለ
አከባቢ እንዲሰፍሩ እያስገደዳቸው መሆኑ ቷውቋል ።
ቀደም ሲል ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ከአከባቢው እንዲፈናቀሉ የተደረጉ ገበሬዎች በከባድ ችግር ላይ መሆናቸውን
መዘገባችን የሚታወስ ነው ።