Friday, April 18, 2014

በአማራ ክልል አዊ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ በፀጥታ አስከባሪ ስም የተሰማሩ የስርአቱ ወታደሮች ንፁሃን ወገኖቻችንን ባልፈፀሙት ወንጀል በመፈረጅ በላያቸው ላይ በደል እያደረሱ መሆናቸው ምንጮቻችን ከቦታው ገለፁ።



በመረጃው መሰረት በአዊ ዞን መስተድደር በሚገኙ ወረዳዎች በስርአቱ የተደራጁ ፀጥታ አስከባሪዎች ከዞኑና ከወረዳው የበላይ ባለስልጣናት በማበር ንፁሃን ወገኖቻችንን ባልዋሉበት ወንጀል በመፈረጅ እያሰርዋቸውና እየደበደብዋቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው ይህ በንፁሃን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍም አገር እየመራሁ ነኝ ከሚል መንግስት የሚጠበቅ ተግባር እንዳልሆነ የአካባቢው ነዋሪዎች ምሬታቸው ገልፀዋል።
 መረጃው በመቀጠል በጃዊ ወረዳም የዞኑና የወረዳው የበላይ ባለስልጣናት በፀጥታ አስከባሪዎች ስም ከተሰማሩ የስርአቱ ሃይሎች ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ህዝብ በማስፈራራት ገንዘብ እያስከፈሉትና እየደበደቡት መሆናቸው ከአካባቢው በተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችለዋል።
   ተገቢ ባልሆነ መንገድ ገንዘብ እንዲከፍሉ ከተደረጉ ነዋሪዎች ውስጥ፣-
-    አቶ ወርቁ አድማሴ 28 ሺ ብር ከአቦ ቀበሌ
-    አቶ ጌታቸው ፋንታሁን 25 ሺ ብር። ከአቦ ቀበሌ
-    አቶ አምሳሉ ቸኮል 27 ሺ ብር  ከወርቅ አገር ቀበሌ
-    አቶ ጌታቸው ገነት 20 ሺ ብር  ከወርቅ ሃገር ቀበሌ
-    አቶ ብዙ አዮህ አድማሴ 48 ሺ ብር ከዘረ-ገነት ቀበሌ
-    አቶ በላቸው አረጋው 26 ሺ ብር ከዘረ-ገነት ቀበሌ
-    አቶ አጥናፉ ወሌ 4 ሺ ብር ከዘረ ገነት ቀበሌ
-    አቶ በላይ ሙሉ 10 ሺ ብር  ከቡንጅራ ቀበሌ
-    አቶ አለምነህ ዳኘው 5 ሺ ብር  ከቡንጅራ ቀበሌ
-    አቶ አለሙ አበጀው 20 ሺ ብር  ከቡንጂራ ቀበሌ
-    አቶ አበጀ አስማረ 10 ሺ ብር ደቅ ቀበሌ
-    አቶ አባተ አድጎ 10 ሺ ብር ከደቅ ቀበሌ
-    አቶ ዘገየ 7 ሺ ብር  ከማተባ ቀበሌ
-    አቶ ጌታቸው 6ሺ ብር ከማተባ ቀበሌ መሆናቸውና
እነዚህ ወገኖቻችን ኢንስፔክተር ባድግ በተባለ ፀረ ህዝብ የፖሊስ አመራር ፍርድ ቤት ከምንወስዳቹህ ያልናችሁን ብትከፍሉ ይሻላቹሃል በማለትና አስታራቂ በመምሰል ከዞንና ከወረዳ ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ከ246,000 ብር በላይ ወደ ግል ጥቅማቸው እንዳዋሉት መረጃው አክሎ አስረድተዋል።