አቶ ይሁን ደምመላሽ በታህሳስ 11,2005 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ጭንቅላቱ ላይ በጥይት ተደብድቦ ህይወቱ
ያለፈው ፤ በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች አባላት ክንዴ ይርሁ ፤ ደሳለኝ ማሞ ፤ ኮንስታብል ለአለምና ሌላ ለግዜው ስሙ ያልታወቀ አራተኛ
ግለሰብ በተተኮሰበት ጥይት መሆኑ በቁጭ ወረዳ ፤ ከአሰስ ወይንማ ቀበሌ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
ባለፈው ሳምንት የከተማዋ ኗሪዎች ጉዳዩን ወደ እሚመለከተው የክልል ባለስልጣናት ለማቅረብ 8 አባላት ያሉት
አንድ ኮሞቴ አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው።