Sunday, October 23, 2016

በአንድ ራስ ሁለት ምላስ



እርግጥ ነው ለአንድ  አገርና ህዝብ  ሰንደቅ ኣላማ ዋነኛው የክብርና የላአላዊነት ቀንደኛ  መለያ መሆኑን  የሚያረጋግጥለት  የከበረ ትርጉም ያለው ከመሆን በላይ  በኣገሪቱ የሚገኙ ብሄር ብሄረ ሰቦች በብዙህነታቸው  በተረጋጋ  ሰላም በኣንድነተቻው፤ በመቻቻልና ፤በወንድማማችነት  የተመስረተ ዲሞክራስያዊ መብቶቻቸውን ተጠቅመው   በባንዴራ  ቀን  የኣገር ፍቅር  በቡዱን መግለፅ ባህርያዊ ነው።       
 ቢሆንም ግን በየጊዜው  ወደ ስልጣን  ከሚወጡ የህዝብን ፀር የሆኑ የአገር መሪዎች  በደምና በአጥንታቸው  ጠብቀው  ኣረንጋዴ ብጫና ቀይ ቀለሞች የፅናትና የጀግኖች የሆነች ባንዴራ እንደፈለጉ በላይዋ ላይ ምልክቶችን በመለጠፍ  ለፖለቲካ  ሸቀጥ እንድትውል ኣድርገውታል።  
 ያለፉት ጨቋኝ ስርአቶች ትተን  ያለፉት ፀረ ዲሞክራሲ ባህሪ የተላበሱ የአምባገነን  ወላጆቻቸው  ኣካሄድ  ተመርተው  ህዝብ ሳይወክላቸው  በብረት ሃይል ኣፍኖ  በሞት ኣፋፍ ላይ ሁኖ ህዝብን በመጨፍጨፍ ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርአት ስናይ የባንዴራ ክብር ተዋርዶ በኢትዮጵያ ብሄር ብሄር ህዝቦች  ጥላቻና መቀቃር  በመፍጠር አንድነታቸው በማመሰ  በባንዴራ ስም የኢትዮጵያ ህዝብ ስላም አንድነት  በፍቅር  ይኖራል  በማለት ሲቀልድ ኣመታት ኣስቆጥረዋል።
  ስልጣንን በሃይል ተቆጣጥረው አገርንና ህዝብን  ወደ ጥፋትና  ኋላ ቀርነት  የሚመሩት የኢህአ ዴግ  ባለስልጣኖች   ዛሬ ባንዴራ እያሉ ደጋግመው መዝሙር ሲዘምሩ ይሰማሉ፣      ነገር ግን በአያቶቻቻንና በአባቶቻችን ተከብራና ታፍራ የቆየችና የነፃነትና የጀግንነት ማሳያ በሆነችው ባንዴራችን ላይ ምንም ክብር  የላቸውም።    
ለዚህ ማስረጃ ሊሆነን የሚችል  የእትዮጵያ  ጠቅላይ ሚኒስተር የነበሩት  ኣቶ መለስ ዜናዊ በኣንድ ኣጋጣሚ    ሲናገሩ ባንዴራ ጨርቅ ናት ብለው መናገራቸው  ከትምክህት የመነጨ በቂ መረጋገጫ ነው።   
 በአንድ ራስ  ሁለት ምላስ  ለማለት የቻልነው ለዚህ ሲሆን ትናንት ጨርቅ ናት ብለው ያንቋሸሽዋት ባንዴራ ዛሬ ተገልበጠው   ኣክባሪ  መስለው የኣዞ  እንባ  ቢያነቡ የሚያስገርም ኣይደለም።
    ይህች ባንዴራ የህዝባችን ማንነት መገለጫና  ክብርዋ በደም  ተጠብቆ  የአገራችን አርማና ምልክት  ሰለሆነች  ልክ የኢህ አዴግ መሪዎች እንደሚሉት  በስልጣን እስካሉ ድረስ የምትኖር  ከሌሉ ደግሞ  የሚያበቃላት  ሳትሆን  በደምና በአጥንት  ለዘመናት ተከብራ የቆየችና ቀጣይም በኢትዮጵያ ህዝብ  ክብርዋ ተጠብቆ የምትኖር ባንዴራ ናት።
 ዛሬ የኢህዴግ  መሪዎች  በፈጠሩት ፀረ ዲሞክራሲ የሆነ  ኣካሄዳቸውና በመልካም አስተዳደር እጦት አገራችን ኢትዮጵያ   በከባድ ግርግር፤ ደም መፋሰስና  በድርጅቶች ውድመት  ባለችበት ግዜ ህዝብችን ከ እስከ እንዳይንቀሳቀስ  የ6ት ወር  የሚቆይ ኣዋጅ በማወጅና እንደዚሁም  ኣመት በመጣ ቁጥር  የባንዴራን ቀን  ምክንያት በማድረግ  ትርጉም በማያመጣ  ዛሬም ህዝብን ሰብስበው  ለ9ኛው ግዜ   ሰደሰኩሩና   መግለጫ ሲያወጡ ተሰምተዋል።
 ይህ ዛሬ የሚከበረው የባንዴር ቀን ልዩ የሚያደርገው የኢህአዴግ ስርአት በህዝብ ላይ የሚያደርስው ግፍና ጭፍጨፋ ህዝባችን ስለ ከፋው በላያቸው ላይ ያነሳው ኣመፅና ትግል ለመግታት ብለው የከፋ የወታደራዊ አስተዳደር ኣዋጅ በማወጅ  ህዝባችን በማጀት ስለ አስገቡት የባንዴር  ቀን  በመከላከያ ሰራዊት ብቻ ተከብሮ እንዲያልፍ ተገደዋል።
 ምንም እንኳ በልጆችዋ ደም ለዘመናት  እየተውለበለበች የመጣች ባንዴራ  አሁን  ግን ለግል   ለኢህአዴግ መሪዎች  ጥቅምና መሳርያ ተብሎ የአገርና የህዝብ ፍቅር ያለው ዜጋ እንዳያከብራት ቢያደርጉ  ህዝባችን ግን በኣምባገነኖች ክብሩና ማንነቱን የሚገልፅበት እውነተኛ የባንዴሬ ቀን የሚከበርበት ኢህ አዴግ ከስልጣኑ ተወግዶ ህዝባዊ የሆነ መንግስት ሲኖር መሆኑ ኣምኖ በመረባረብ ላይ ይገኛል።
  በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ  እንዳለፈው  ሁሉ  ስለ ባንዴራና አገር ብለው  የውስጥና   የውጭ   ባእዳውያን  ወራሪዎች እየመከቱና መስዋእት እየከፈሉ ተከብራ  እንድትቆይ  ያደርጉ  ዛሬም እንደ ትናንቱ  ጸረ ህዝብና ፀረኣገር የሁኑት የኢህአዴግ መሪዎች  ከስር መሰረታቸው ተጥለው  የሚወገዱበት ግዜ ሩቅ ኣይሆንም።
  ያን ግዜ የሉኣላዊነቱ፤ የአንድነቱና የማንነቱ መገለጫ የሆነችው ባንዴራ በተረጋጋ ሰላም ሆኖ ከወንድሞቹ ከሁሉም የኢትዮጵያ ብሄር ብሄር ሰቦች በሰላም በፍቅርና  በወንድማማችነት ኣብሮ ደስታውን የሚገልፅበት ግዜ ለማቀላጠፍ  የሚያካሂደው ትግል  የስርአቱ ፀረ ህዝብ ተግባር  ሳያግደው ትግሉ ኣበርትቶ  ሊቀጥልበት ይገባል።


No comments:

Post a Comment