በደረስን ዘገባ መሰረት የወረዳዋ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ስብሰባ የተጠራው ከመስከረም 2005ዓ/ም
ጀምሮ ምን ሰራን? በሚል የስራ ግምገማ ለማድረግ ሲሆን ሰራተኞቹ በአንጻሩ ቅድሚያ መታየትና መመለስ የሚገባው የሰራተኞች የደሞዝ
ጭማሪ ጥያቄ መሆን አለበት ሲሉ መጠየቃቸውን ለማወቅ ተችሏል።
ሰራቶኞቹ በወረዳዋ ተመድበው በሚሰሩባቸው የተለያዩ አከባቢዎችም መድሃኒት እንደሌለና በፋርማሲ አለ የሚባለው
መድሃኒትም ቢሆን ግዜው ያለፈበትና በሚመለከተው አካል ክትትልና ቁጥጥር ስለማይደረግለት ኗሪው ህዝብ በአከባቢው ወድሚገኙ ህክምና
በመሄድ ትክክለኛ መድሃኒት ማግኘት ሲገባው ጊዜው ያለፈበት መድሃኒት እየወሰደ ለሌላ ተጨማሪ በሽታ የሚጋለጥበት ሁኔታ መኖሩን አስረድተዋል።
በተመሳሳይ በወረዳዋ በሚገኙ 20 ጣቢያዎች ኗሪ ህዝብ ከታህሳስ 15,2005 ዓ/ም ጀምሮ “ዘመቻ መለስ
ለእድገት” በሚል መሪ ቃል በየሳምንቱ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲወጣ መገደዱን ለማወቅ ተችሏል።