በደረሰን ዘገባ መሰረት አቶ መልሰው አበራ ታህሳስ 10,2005 ዓ/ም ከቀኑ 8፣00 ሰዓት በግፍ የተገደለ
ሲሆን ታህሳስ 11,2005 የቀብር ስነስርዓቱ ተፈጽሟል ። ግለሰቡ ህይወቱ ያለፈው ኮንስታብል ገብረኪዳን ይገረሙና ሚሊሽያ መዝገቡ
ባየን የተባሉ የመንግስት ታጣቂዎች የገደሉት ሲሆን ወንጀሎኞቹ እስካሁን ድረስ ወደ ህግ ቀርበው አልተጠየቁም ።ሁኔታው በአከባቢው
ኗሪዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥራል።
ድርጊቱ ከግዜ ወደ ግዜ ህዝባዊ ተቀባይነቱን እያሽቆለቆለ የመጣ የኢህአደግ መንግስት በተቋዋሚ ድርጅቶች
መጠናከር ስጋት ላይ ስለወደቀ አለሁ ለማለት ህዝብን በጠመንጃ ሃይል ለማንበርከክ እየወሰደው ያለ የቀቢፀ ተስፋ እርምጃ ነው ሲሉ
አንዳንድ ወገኖች ይናገራሉ።
ባለፈው
ሳምንት ባቀረብነው የዜና ዘገባ አቶ ደምመላሽ የተባለ ንፁህ ዜጋ አሸባሪ በሚል ሰበብ ከመንግስት ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት ህይወቱ
ማለፉ መዘገባችን የሚታወስ ነው።