በሁለቱ ብሄር ተወላጆች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መካከል የተቀሰቀሰው ግጭት በሽንት ቤት ግድግዳ ላይ ‘ጋላ’
የሚል ስድብና ሌሎች አስጸያፊ ቃላቶች ተጽፈው በመገኘቱና ጸሃፊዎቹም የብሄረ አማራ ተወላጆች ናቸው በሚል ምክንያት ከቀኑ 10፣00
ሰዓት የብሄረ ኦሮሞ ተወላጆች በብሄረ አማራ ተወላጆች ላይ ድንጋይ መወርወር በመጀመራቸው መሆኑ ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት የብሄር አማራ ተወላጆች ቀደም ብለው በሽንት ቤት ተጽፎ የነበረውን ጋላን ጨምሮ ሌሎች አስጸያፊ ቃላቶች ሌላ ቀለም ተጠቅመው ለማጥፋት የተለያዩ ሙከራ
ቢያደርጉም የብሄረ ኦሮሞ ተወላጆች በበኩላቸው የተጻፈውን ነገር ሁሉም ሰው እንዲያየው በሚል ከላይ የተቀባውን ቀለም በማስወገድ
እንዲታይ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችለዋል።
በግጭቱ 20 ተማሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ሁለት ተማሪዎች ሆስፒታል እንዲገቡ
ተድርጓል። ሆስፒታል ከገቡት አንዱ ተማሪ ታህሳስ 26,2005 ዓ/ም ህይወቱ ያለፈ ሲሆን ሁለተኛው የተጎዳው ጭንቅላቱ አከባቢ ስለሆነ
ጤንነቱ በአሳሳቢ ሁኔታ ላይ ይገኛል።
በግቢው ውስጥ በተነሳው ግጭት ምክንያት የመመገብያ አዳራሽና የተማሪዎች መኝታ ቤት የመስኮት መስታዎት የተሰባበረ
ሲሆን በግቢው ውስጥ ቆመው ከነበሩት የፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስን ጨምሮ በሌሎች ሦስት መኪናዎች ላይ ጉዳት ደርሳል።
ግጭቱን ቀስቅሰዋል በሚል ከ 100 በላይ ተማሪዎች ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ተወስደው የታሰሩ ሲሆን ወደ አራት
ኪሎ ግቢ በሚገቡና በሚውወጡ ተማሪዎችም ፍተሻ እየተደረገ ነው። የፌደራል ፖሊስ ከአራት ኪሊ ጀምሮ እስከ ስድስት ኪሎ ባለው መስመር
ተሰማርቶ ጥበቃ እያደረገ መሆኑ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ ጭምሮ ያስረዳል።
የተከሰተው ግጭት የስርዓቱ እጅ ሊኖርበት እንደሚችል አንዳንድ ወገኖች ይገልጻሉ።