ህወሓት ከዚህ ቀደም በትግራይ ህዝብ ላይ የሰራውን ግፍ እንዳይበቃ አሁን ደግሞ ገደል አፋፍ ላይ ያለችውን
ስልጣኑን ለማቆየት ከወረዳ በላይ የሚሊሽያ ሃላፊዎችን አስገድዶ በማሰባሰብ በጥቅምትና ህዳር 2005 ዓ/ም በመቐለ ወታደራዊ ስልጠና
እንዲወስዱ አድርጓል። ሚሊሽያዎቹ በሁኔታው ደስተኞች እንዳልሆኑ ከተሳታፊዎቹ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በድምበር አከባቢ የሚገኙ የሚሊሽያ አባላት አካባቢያቸውን እራሳቸው እንዲጠብቁ ፥
በማሃል የሚገኙት የሚሊሽያ አባላት ደግሞ በተለያዩ ምክንያት ከመከላከያ የከዱ የሰራዊት አባላትን መተካት ይችሉ ዘንድ ወታደራዊ
ስልጠና እየተሰጣቸው ቢሆንም እነሱም ስልጠናውን በማቃረጥ ወደ መረጡት ቦታ በመሸሽ ላይ መሆናቸውን ለማወቅ ተችለዋል።
መንግስት የሚሊሺያ አባላትን በግዳጅ ለማሰልጠንና በወታደራዊ ስራ ለማሰማራት ቢሞክርም ሚልሽያዎቹ ነገሩን
ከልብ ስላላመኑበት ህወሓት ተከታታይ ቅስቀሳ ለማድረግ ተገዷል። ቢሆንም
እቅዱ እንደ ታሰበለት ሊፈጸም እንዳልቻለ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።