መንግስት ስልጣኑን በወታደራዊ ሃይል ለማሰንበት ካለው ፍላጎት አንጻር ከተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ሚሊሽያዎችን
አግባብቶ ለማሰልጠን የነደፈው ውጥን ተቋውሞ ስላጋጠመው ተግባራዊ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል። አሁን አሁን ግን ሃይል በመጠቀም የሚሊሽያ
አባላትን በማስገደድ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስዱ ሙከራ ማድረግ ጀምሯል። ሆኖም ሚሊሽያዎቹ ስልጠናውን ከልብ ስላልተቀበሉት ከስልጠናው
በየግዜው እንደሚጠፉ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።
በደረሰን ዘገባ መሰረት በያዝነው ሳምንት በታሕታይ አድያቦ ወረዳ በግዳጅ ወታደራዊ ስልጠና እንዲወስድ የተደረገ
አንድ ሚሊሽያ እራሱን ሲያጠፋ ሌሎች ሁለት ደግሞ በከባድ ቆስለው ህይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ቷውቋል።
ቀደም
ሲል በክልሉ የሚገኙ የሚሊሽያ አባላት በኢህአደግ መንግስት የቀረበላቸውን ወታደራዊ ስልጠና መቋወማቸው መዘገባችን የሚታወስ ነው።