Wednesday, March 13, 2013

በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በቀበሌ 03 ህገ-ወጥ በሚል ሰበብ ቤት እንዲያፈርስ የተላከ አፍራሽ ግብረሃይል ከአከባቢው ኗሪዎች ጋር ተጋጨ፣




በከተማዋ 03 ቀበሌ የሚገኙ 20 በ 20 መኖርያ ቤቶች ህገ-ወጥ ስለሆኑ መፍረስ አለባቸው በሚል የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ሃላፊ ተክላይ የተባለ ካድሬ አራት የፖሊስ አባላት ፤ አራት መሃንዲሶች ፤ ቤት አፍራሽ ሃይልና የአከባቢው የመስተዳድር አካላት ጋር በመሆን ቤቶችን ማፍረስ ሲጀምሩ የአከባቢው ኗሪዎች አንድ ላይ በመውጣት በመቃወማቸው ግጭት ተቀስቅሶ አንዳንድ የመስተዳድር አካላት በሁኔታው ተደናግጠው ሮጠው ሲያመልጡ ከግጭቱ ማምለጥ ያልቻሉት በደረሰባቸው ጉዳት በምድረ ገነት ሆስፒታል ገብተው በመታከም ላይ እንደሆኑ ለማወቅ ተችለዋል፣
ግጭቱን ተከትሎ ህዝቡን አነሳስተዋል በሚል በቁጥጥር ስር ከዋሉ 15 ሰዎች መካከል እስካሁን ድረስ ስምንት ሰዎች በህዝብ ተቃውሞ የተፈቱ ሲሆን በ 03 ቀበሌ የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞም ወደ 01 እና 04 ቀበሌዎች ተስፋፍቷል፣ በሁኔታው የተደናገጠው የኢህአዴግ መንግስት በከተማዋ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትን በማሰማራት ያሰጋሉ በተባሉ ቀበሌዎች  ተደራጅተው ፓትሮል በማድረግ ላይ መሆናቸውን ከከተማዋ የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣