በደረሰን ዘገባ መሰረት ኩማ ሚደቅሳ አቶ በላይነህ ክንድያ ከተባሉ ነጋዴ ጉቦ መቀበላቸውን ቢረጋገጥም ፦
ጉቦ ሰጭው ነጋዴ ጉቦ በመስጠት ወንጀል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን ጉቦ ተቀባዩ ኩማ ደመቅሳ ግን በዚሁ ጉዳይ እስካሁን ድረስ የቀረበላቸው
ክስ እንደሌለ ለማወቅ ተችለዋል፣
በመንግስት ሆቴሎች ኤጄንሲ ሲተዳደር የነበረ ኢትዮጵያ ሆቴል ለአቶ በላይነህ መሸጡ የሚታወቅ ሆኖ ሆቴሉ
አሁን ባለበት ሁኔታና ቦታ የባለ አራት ሆቴል መስፈርትን ስለማያማላ ፈርሶ በ 1700 ካ/ ሜትር እንደአዲስ እንዲሰራ ትእዛዝ እንደተሰጠና
ለእድሳት የሚሆን ሁለት ሚልዮን ብርም ነጋዴው እዲያቀርቡ መመሪያ መሰጠቱን ለማወቅ ተችለዋል፣
በተመሳሳይ
የአያት ኮንስትራክሽን ሃላፊ የነበሩት አቶ አያሌው ተሰማ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ መኖርያ ቤታቸውን በመፈተሽ ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ
የተወረሰ ሲሆን እሳቸውም መጋቢት 16,2005 ዓ/ም በ 21 ወንጀሎች ተከሰው በእስር ቤት እንደሚገኙ ቷውቋል፣