የሽረ-እንዳስላሰ ከንቲባ ፍስሃ ውበት ፤ ኗሪነቱ በከተማዋ የሆነ ሻምበል ኪሮስ ፍስሃ የተባለ ከሰራዊት
የተሰናበተ አንድ ግለሰብ በህጋዊ መንገድ ያገኘውን መሬት በወረራ የተያዘ ነው በማለት ባለመብቱ መሬቱ እንዲነጠቅ በማንአለበኝነት
ቢወስንም ጉዳዩን ወደ ህጋዊ ፍርድ ቤት ቀርቦ ህጋዊ መሆኑን ሊረጋገጥ ችሏል፣
ባለጉዳዩ ሻምበል ኪሮስ በካድሬው የተሰጠውን ህገ ወጥ ውሳኔ በመቃወም ፍስሃ ካሕሳይ የተባለ የህግ ጠባቃ ቀጥሮ ጉዳዩን በህጋዊ ፍርድ ቤት እንዲታይ በማድረግ
መሬቱን በአግባቡ የገዛው መሆኑን ተረጋግጦ የተነጠቀው መሬት እንዲመለስለት ተወስኖለታል ፣ ነገር ግን በተሰጠው ብይን የተቆጣ የከተማዋ
ከንቲባ ዳኞችን እቢሮው ድረስ በማስጠራት እንዲህ ያለውን ውሳኔ እንድትወስኑ ማን ነው ያዘዛችሁ ? በማለት በማስፈራራት ጉዳዩን
እንደ አዲስ እንዲታይ ባዘዘው መሰረት ጉዳዩ ዳግም እንዲታይ ቀጠሮ መያዙን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ዳኞች
ከማንኛውም ጫና ነጻ ሆነው ለህግና ለህሊናቸው ብቻ ታማኝ በመሆን በሚቀርቡሏቸው ማናቸውም ጉዳዮች ፍትሃዊ ውሳኔ መስጠት እንዳለባቸው
የታወቀ ቢሆንም የኢህአዴግ ስርዓት የህግ የበላይነትን በመተላለፍ ፍትህን ማዛባት የተለመደ ተግባር አድርገውታል፣