Monday, June 3, 2013

በባህርዳር ከተማ በሚገኘው ያለምብርሃን ሆስፒታል ከ 200 በላይ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች የሆስፒታሉን ብልሹ አሰራር በመቃወም ጉንበት 17,2005 ዓ/ም ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፣



የሰላማዊ ሰልፉ ዋና ምክንያት በሽተኞች ህክምና ፍለጋ ወደ ሆስፒታል በሚመጡበት ጊዜ ተገቢውን ህክምና ማግኘት ሲገባቸው የሆስፒታሉ አሰራር በጉቦና ወገን የተተበተበ በመሆኑና በተለይም ራቅ ካለው ገጠር የሚመጡት በሽተኞች በወቅቱ የህክምና አገልግሎት አያገኙም የሚል ሲሆን ችግሩ ክወዲሁ ታይቶ መፍትሄ እንዲደረግለት ለመጠየቅና እስኪቀረፍ ድረስም ተቃውማቸውን አጠናክረው እንደሚቀጡልበት የሰላማዊ ሰልፉ ተሳታፊዎች ግልጽ አድርገዋል፣
አድማው መንግስት በመላ አገሪቱ የሚከተለውን ብልሹ አሰራርን የሚቃወም ሆኖ፣ በተለይ በባህርዳር ከተማ የሚካሄድ ማንኛውም እንቅስቃሴ ህዝቡን ማእከል ያደረገ አለመሆኑንና የስርዓቱ ባለስልጣናት ያላቸውን ሃላፊነት አለአግባብ በመጠቀም የሃገርንና የህዝብን ሃብት እየዘረፉ እራሳቸውን ለማበልጸግ እየተከተሉት ያለ ብልሹ አሰራር እንዲታረም ጠይቃል ፣ መላው የባህርዳር ከተማ ኗሪም ተቃውመውን መደገፉን ቷውቋል፣