Monday, June 3, 2013

መንግስት ከትህዴን ጋር ትተባበራላችሁ በሚል ሰበብ በላዕላይ አድያቦ ኗሪዎች ላይ የተለያዩ በደሎችን መፈጸሙን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣



በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ በላዕላይ አድያቦ ወረዳና አከባቢዋ የሚኖሩ ዜጎችን ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ግንኝነት አላችሁ ፤ መንገድ በመምራት ፤ እህል ውሃ በመስጠት ትተባበርዋቸው አላችሁ በማለት በስርዓቱ ካድሬዎችና የጸጥታ አባላት በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
ከትህዴን ጋር ግንኝነት አላችሁ በሚል ሰበብ ጉንበት 5,2005 ዓ/ም ከሞነሪያ ቤታቸው በጸጥታ ሃይሎች ታፍነው ከተወሰዱት የአከባቢው ኗሪዎች መካከል አቶ ነጋሲ ዮዋሃንስ የሚገኙባቸው ሲሆን እስካሁን ድረስ ያሉበትን አድራሻ እንደማይታወቅ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣
የትህዴን እንቅስቃሴ ከትግራይ ክልል አልፎ በመላው ኢትዮጵያ መስፋፋቱን የተገነዘቡ የስርዓቱ ባለስልጣናት በሁኔታው ተደናግጠው ያገኙትን ሰው ሁሉ የትህዴን አባል ነው በሚል ማዋከብ ስራችን ብለው ተያይዘውታል፣