የባህርዳር ከተማ ኗሪዎች እንደሚሉት በከተማዋ አንድ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-00746 የሆነ ቮልቮ የጭነት መኪና
ጭኖት የነበረ ከአባይ ግድብ የተዘረፈ ስሚንቶ በአቶ ይልማ ማሩ መጋዝን አራግፎ ሲወጣ ጉንበት 30,2005 ዓ/ም በከተማዋ ኗሪዎች
እጅ ከፈንጅ የተያዘ ሲሆን በተመሳሳይ የሰሌዳ ቁጥሩ 3-05704 የሆነ መኪና ጭኖት የነበረውን ላሜራ አራግፎ ከቦታው ማምለጡን
ለማወቅ ተችሏል።
በሌላ ዜና በሰ/ምዕራብ ትግራይ ትኩረት ያጣው የሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ መጥቶ በአሁኑ ወቅት ፍጹም አገልግሎት በማይሰጥበት ደረጃ ላይ ደርሳል በከተማዋ ንጹህ የመጠጥ ውሃ ከጠፋ
ሁለት ሳምንት ያስቆጠረ ሲሆን የከተማዋ ኗሪዎች በሁኔታው ክፉኛ መማረራቸውን ቷውቋል ።
የክልሉ
ባለስልጣናት በትግራይ በንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት እጦት የሚሰቃይ ኗሪ ከእንግዲህ አይኖርም በማለት ቢደሰኩሩም በተግባር ግን
የክልሉ ኗሪ ንጹህ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ስለማያገኝ ንጽህናውን ያልጠበቀ የጉድጓድ ውሃ በመጠጣት ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች
ሲዳረጉ ይታያሉ።