Friday, June 14, 2013

መንግስት በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የጀመረውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ተግባር አጠናክሮ ቀጥሎበታል።



በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በመጭው ሰኔ 7,2005 ዓ/ም በከተማዋ መስተዳድር እንዲፈርሱ የተወሰነባቸው 68 የመኖሪያ ቤቶች ባለቤቶቹ ውሳኔውን አውቀው ቀድመው በራሳቸው ጊዜ እንዲያፈርሱ ካልሆነ ግን መንግስት ዶዘር በምሰማራት መኖሪያ ቤቶች ከነንብረታቸውንም ቢሆን ለማፍረስ ይገደዳል የሚል መመሪያ ማውረዱን ቷውቋል።
ከከተማዋ መስተዳድር የወረደው ቀጭን ትእዛዝ ኗሪዎቹ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ እንጂ ምንም ዓይነት ጥያቄ እንዲያቀርቡ የሚፈቅድ ባለመሆኑ ኗሪዎቹ በተለይም ቤታቸው እንዲፈርስ የተወሰነባቸው ዜጎች አቤት የሚሉበት ቦታ ኣጥተው በጭንቀት ተውጠው ይገኛሉ።
ይህ በእንዲህ እያለ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ፤ በዓዲ ራህዋና በሰፍአ መካከል አንድ የኢህአዴግ ስርዓት ታጣቂ ሚሊሽያ በስድስት ጥይት ተደብድቦ በዚሁ ሳምንት ሞቶ የተገኘ ሲሆን በሁኔታው የተደናገጡ የስርዓቱ የጸጥታና የመስተዳድር አካላት በመዳበና ገዛ መቐር አከባቢ የሚገኙ የኩናማ ብሄረሰብ አባላትን በመሰብሰብ ገዳዮቹ በውስጣችሁ ነው ያሉት አስወጣቸው በማለት እያስፈሯሯቸው መሆኑን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።