በደረሰን ዘገባ መሰረት አብዛኛውቹ ከቀበሌ 03 የተወሰኑት ደግሞ ከቀበሌ 02 በድምሩ በከተማዋ ከ
173 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ከከተማዋ የመስተዳድር አካላት በተሰጠ ትእዛዝ መሰረት በያዝነው ሳምንት ብቻ በዘመቻ በዶዘር እንዲፈርሱ
ተደርጓል ። ህጻናትና ሽማግሌዎች የሚገኙባቸው ከ 80 በላይ ቤት አልባ እንዲሆኑ የተፈረደባቸው የከተማዋ ኗሪዎች ከነንብረታቸው
በጎደና ላይ ወድቀው ቀን በጸሃይ ማታ በብርድ በመሰቃየት ላይ ይገናሉ።
ተፈናቃዮቹ ተለዋጭ ቦታና ካሳ ሳይሰጠን ከመኖሪያ ቤታችንን አንነሳም በማለት ወደ አከባቢው ከተላከው ቤት
አፍራሽ ግብረ ሃይል ጋር ግጭት ፈጥረው እስካሁን ድረስ ቁጥራቸው ያልታወቁ በርካታ ሰዎች በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች የተቀጠቀጡና
የታሰሩ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።