Wednesday, June 5, 2013

በተለያዩ የሃገሪቱ ከተማዎች የሚገኙ ወጣቶች ኢህአዴግን ባለመደገፋቸው ብቻ ግፍና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ቷውቋል።



ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው ከስራ እጥነት መውጣት ያልቻሉ በአሩሲ ፤ ወለጋ ፤ ባቲ ፤ በበዴሌና ሌሎች ከተሞች ኗሪ የሆኑ በርካታ ወጣቶች ስራን ማግኘት ከፈለጉ በአንድ ለአምስት አደረጃጀት እንዲደራጁና የኢህአዴግ አባል እንዲሆኑ ከስርዓቱ ካድሬዎች የቀረበላቸውን ሃሳብ ውድቅ አድርገውታል።
ወጣቶቹ ከስርዓቱ የቀረበላቸውን ሃሳብ ባለመቀበላቸው ምክንያት ጸረ-ልማት ፤ አሸባሪ ፤ ዘራፊዎች የሚል ስም እየተሰጣቸው በአሁኑ ጊዜ ከየመኖሪያ ቤታቸውና ከሚንቀሳቀሱበት አከባቢ እየታፈኑ እንዲወሰዱ በማድረግ ባልታወቀ ስውር ቦታ የተለያየ ስቃይና በደል እየደረሰባቸ መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
አምባገነኑ የኢህአዴግ ስርዓት ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ወጣቶች በተመረቁበት ሞያ ሃገራቸውንና ህዝባቸውን እንዳያገለግሉ ማድረግ ሲገባው የገዥው ፓርቲ አባል ባለሆናቸው ብቻ የስራ እድል በመንፈግና በጠላትነት በመፈረጅ ያለ ፍርድ ቤት ትእዛዝ በርካታ ወጣቶች በየእስር ቤቱ ታጉረው እንዲማቅቁ እያደረገ ሲሆን ፥ ከእስረኞች መካከል አንዳንዶቹ የተገደሉ ሲሆን ገና ተመሳሳይ እጣ የሚጠብቃቸው መኖራቸውም ለማወቅ ተችሏል።