በታሕታይ አድያቦ ወረዳ የዓዲ-አሰር አከባቢ ኗሪዎች ከትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ትህዴን) ጋር
ይተባበራሉ የሚል ስጋት ያደረባቸው የወረዳዋ የመስተዳድር አካላትና የጸጥታ ሃይሎች በእያንዳንዱን ኗሪ እንቅስቃሴ ላይ የቅርብ ክትትል
እንዲደረግ መመሪያ ማውረዳቸውን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ ከወረዳዋ የተላኩ የፖሊስ አባላትና የዓዲ-አሰር የሚልሽያ አባላት አንድ ላ
በመሆን በድንገት አሳቻ መንገድ በመጠበቅ የት እየሄድክ ነው ? ከየት እየመጣህ ነው ? ከማን ጋር ተገናኘህ? በማለት የኗሪውን
የመንቀሳቀስ ነጻነት በመግፈፍ እይሰቃዩት መሆኑን ቷውቋል፣
እንዲህ
ባለው ህገ-ወጥ አሰራር ጉንበት 18,2005 ዓ/ም አቶ ፍስሃ ብርሃነ የተባለ የዓዲ-አሰር ኗሪ የፈጸመው ምንም ወንጀል ሳይኖር
ከትህዴን ጋር ትገናኛለህ በሚል ሰበብ በግለሰቡ ላይ ተኩስ በመክፈት በቁጥጥር ስር በማዋል በወረዳዋ ፖሊስ ጣቢያ አስረው እያሰቃዩት
መሆኑን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣