Wednesday, June 12, 2013

እየተመናመነ የመጣውን የኢህአዴግ ሰራዊት ለማጠናከር ሲባል በየአከባቢው አዲስ ምልምሎችን ለመመልመል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፣



ከሰሜን እዝ ከ 19ኛ ና 20ኛ ክ/ጦሮች የጉንበት 2005 ዓ/ም ደምዎዝ ከተቀበሉ ብሁዋላ በርካታ ወታደሮች የከዱ ሲሆን አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ሬጅመንት ብቻ በአማካይ ስድስት ወታደሮች እንድሚጠፉና ከየክ/ጦሩም የጠፉትን ፍለጋ ተመድበው የሚላኩ ወታደሮች መኖራቸውንም ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላል፣
ወታደሩ ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ተጠቅሞ ጦሩን የሚከዳበት ዋና ምክንያት መጀመሪያ ሲመለመል የተገባለትን ቃል ስለማይተገበርና በሰራዊቱ የመተዳደሪያ ህግ መሰረት የመሰናበት መብቱንም ስለማይጠበቅለት ነው ሲሉ የበታች አመራሮች ለበላዮቻቸው በድፍረት ይናገራሉ በዚህም በአመራሮች መካከል አለመተማመን መፈጠሩን ቷውቋል፣
ክዳት በሁሉም የመከላከያ ሰራዊት ክፍሎች የሚታይ ሆኖ የተመናመነውን የሰው ሃይል ለመሙላት የትግራይ ክልል ፖሊስ ሃላፊ ወዲ ሻምበል የሚገኝበት በርካታ የክልሉ ባለስልጣናት አዲስ ሰራዊት ለመመልመል እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው ። እንቅስቃሴው በደቡብ ትግራይ ከህዝብ በተነሳው ተቃውሞ ሊሳካ እንዳልቻለ የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያመለክታል፣