Sunday, June 9, 2013

መንግስት በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የጀመረውን መኖሪያ ቤቶችን የማፍረስ ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



በደረሰን ዘገባ መሰረት በሽረ እንዳስላሰ ከተማ ቁጥራቸው እስከ 83 የሚደርሱ በ01 ቀበሌ የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን በያዝነው ሳምንት እንዲፈርሱ በከተማዋ ከሚገኙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ቀጥተኛ መመሪያ ወርዷል። በመንግስት በወረደው ትእዛዝ መሰረት መኖሪያ ቤታቸውን እንዲያፈርሱ ከተነገራቸው የከተማዋ ኗሪዎች መካከል
1-አቶ አስመላሽ ማላኺ
2-አቶ ተስፋይ ነጋሽ
3-አቶ አብራሃለይ
4-አቶ ተመስገን ገ/ዋህድ
5-አቶ ሙሩጽ
6-አቶ አጽረጋ የተባሉ ዜጎች ይገኙበታል።
ባሳለፍነው ሳምንት በከተማዋ መንግስት ባሰማረቸው ዶዘሮች ከፈረሱት 173 መኖሪያ ቤቶች ቁራቸው እስከ 80 የሚደርሱ ኗሪዎች ቤት አልባ ሆነው በየጎዳናው ወድቀው ለጸሃይና ለብርድ መዳረጋቸው የሚታወቅ ነው። ህዝቡን ለተቋውሞ ያነስሳሉ በሚል ጥርጣሬ የታሰሩና በጸጥታ ሃይሎች ገና በመፈለግ ላይ ካሉ የከተማዋ ኗሪዎች መካከል
1-አቶ ወላይ መብራህቱ
2-ሃፍቶም ታረቀ
3-ሃፍቱ አብርሃ
4-ተሾመ ወ/ሩፋኤል
5-አዳነ
6-የማነ
7-ኪዳነ
የተባሉ ዜጎች የሚገኙባቸው ሲሆን ግለሰቦቹ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚችል ምንም ዓይነት ወንጀል ባይፈጽሙም ለስርዓቱ አስጊዎች ናቸው በሚል ሰበብ መንግስት በሰዎቹ ላይ እርምጃ ለመውሰድ የሚያደርገው ጥረት መሆኑን ቷውቋል።