Sunday, June 9, 2013

የጋምቤላ ከተማ ኗሪዎች የኢህ አዴግን ስርዓት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።



በጋምቤላ ከተማ የሚታየውንና እስካሁን ድረስ መፍትሄ ያላገኘው የመሰረተ ልማት ችግር እንዲቀረፍላቸው በተደጋጋሚ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት አመልክተው የተሰጣቸው መፍትሄ ባለመኖሩ በሽዎች የሚቆጠሩ የከተማዋ ኗሪዎች ጉንበት 27,2005 ዓ/ም ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ አንድ ላይ በመሆን በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ቅሬታ መግለጻቸውን ቷውቋል።
 ሰላማዊ ሰልፉ በከተማዋ ከሚታዩ ችግሮች ጋር የተያያዘ ቢሆንም በቅርቡ በአ/አበባ ከተማ ከተደረገው በሰማያዊ ፓርቲ የተመራ ሰላማዊ ሰልፍ ግንኝነት እንዳለው ከአከባቢው የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
  መንግስት በሰላማዊ ፓርቲ መሪነት በአ/አበባ ከተማ የተካሄደውን ሰላማዊ ሰልፍ ተከትሎ በሌሎች ክልሎችም ሊቀጥል ይችላል የሚል ስጋት ስላደረበት የተቋውሞ ሰልፍ ሊቀሰቀስባቸው ይችላል በሚላቸው አከባቢዎች በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት በማሰማራት ላይ መሆኑን ቷውቋል።