በዞኑ በጉንበት ወር ብቻ ስድስት የአከባቢው ኗሪዎች ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድለው የተገኙ ሲሆን
፤ ወንጀለኞቹ ሰዎችን ለመግደል የሚገለገሉበት መሳሪያም ፤ ከመንግስት የጸጥታ አካላት በኪራይ መልክ የሚያገኙት ሆኖ ፤ ዘርዝፊዎቹ
ከሟቸቹ የሚገኘውን ገንዘብ ከአከባቢው የጸጥታና የመስተዳድር አካላት ጋር አብረው እንደሚካፈሉት የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።
ይህ በእንዲህ እያለ በሽንዲ ከተማ ሰላማዊ ሰው የገደሉ የስርዓቱ ታጣቂዎች በነጻ መለቀቃቸውን ቷውቋል ።
በአዊ ዞን ሽንዲ ከተማ አቶ ይሁን ደምመላሽ የተባሉ ንጹህ ዜጋን አሸባሪ በሚል ሰበብ ከገደሉት የኢህአዴግ
ታጣቂዎች መካከል፣-
1-ኮንስታብል ብርሃኑ ሽፈራው
2-ኮንስታብል ለአለም
3-ሚሊሽያ ደሳለው ማሙ
4-ሚሊሽያ ክንዴ ይርጉ የሚገኙባቸው ሲሆን ለምን በነጻ ተለቀቁ የሚል ጥያቄ ከህዝቡ እንዳይነሳ ለግዜው
በፖሊስ ቁጥጥር ስር እንዲውሉ በማድረግ መርማሪ ፖሊስ ኢንስፔክተር ደረጀና ዋና አስተዳደር ሙላቱ ጌታሁን የሚገኙበት የአከባቢው
የፖሊስ ጽ/ቤት ፤ አቃቢ ህግና ፍርድ ቤት በመመሳጠር በነጻ እንዲለቀቁ ማድረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል።