Wednesday, July 10, 2013

በአዲስ አበባ ከተማ በመሬት እደላ ስራ በሃላፊነት ተሰማርቶ በጉቦና ጥቅማ ጥቅም ሲሰራ የነበረ አቶ ቃሲም ስዒድ መገደሉን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል።



አቶ  ቃሲም ስዒድ የከተማን መሬት ህጉ በሚፈቅደው መሰረት ለኗሪው ማቅረብ ሲገባው ሃላፊነቱን አለአግባብ በመጠቀም በጉቦና ጥቅማ ጥቅም ነበር የሚሰራው ። በሁኔታው የተናደዱ የአ/አበባ ከተማ ኗሪዎች ሰኔ 26,2005 ዓ/ም ግለሰቡን መግደላቸውን የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል።
በርካታ የከተማዋ ኗሪዎች ለመኖሪያ ቤት የሚሆን የከተማ መሬት ለማግኘት ማመልከቻቸውን በማቅረብ ለብዙ ዓመታት ቢመላለሱም መሬት የሚታደለው ህጉ በሚፈቅደው ሳይሆን ጉቦ ለሚሰጡ ከውጭ ለመጡ ጥቂት ባለሃብቶች ብቻ ነው በማለት ኗሪ በተደጋጋሚ ቅሬታውን ሲገልጽ እንደቆየ የሚታወስ ነው።