ባለው ሃብት በመመካት ቦታና ጊዜን መርጦ በአንዲት ልጃገረድ ላይ አስገድዶ ወሲባዊ ጥቃት በመፈጽም ክብረ
ንጽህናዋን የደፈረ መካንንት ዓሊ የተባለ ግለሰብ ፥ የፈጸመው ከባድ ወንጀል በወቅቱ ተጣርቶ ወደሚመለከተው አካል ቀርቦ ተገቢውን
ውሳኔ እንሰጠው ማድረግ የፖሊስ ስራና ሃላፊነት ቢሆንም በወረዳዋ ከፍትህ ይልቅ ለግል ጥቅማቸው ከቆሙ የፖሊስ አባላት መካከል ኢንስፔክተር
አስማማው ጋሻው ከተጠርጣሪው አስር ሽህ ብር ጉቦ በመቀበል ያለ ምንም ምርመራ ነጻ እንደለቀቀው ከቦታው የደረስሰን ዘገባ ያመለክታል።
በእንጅባራ ወረዳ የሚገኙ የፍትህ አካላት በተለይም የፖሊስ አዛዦችና የምርመራ ክፍል አባላት ለፍትህ የቆሙና ህዝብን ለማገልገል የሚሰሩ ሳይሆን ሃላፊነታቸውን አለአግባብ
በመጠቀም ፍትህን እያዛቡ ግላዊ ጥቅማቸውን ማሳደድ እንድ አንድ መደበኛ ስራ አድርገው ይዘውታል። ጉቦ ለመክፈል ፈቃደኛ ያልሆነ
ወይም አቅም ያጣ የአከባቢው ኗሪ ፍትህ አጥቶ በቀጠሮ ሲመላለስና ሲንገላታ ማየት የተለመደ ሆናል።