Monday, July 8, 2013

በሰሜናዊ ምዕራብ ትግራይ ዞን ፤ በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ሙስናን እንዲያጣሩ በጸረ-ሙስና ኮሙሽን የተመደቡ ሰራተኞች በሙስና ቅሌት መዘፈቃቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣




በደረሰን ዘገባ መሰረት በታሕታይ አድያቦ ወረዳ ሦስት ሚልዮን ብር የህዝብ ገንዘብ ዘርፈዋል በሚል ታህሳስ 7,2005 ዓ/ም በሙስና ወንጀል በጸረ- ሙስና ኮሙሽን ክስ ቀርቦባቸው በእስር ላይ የነበሩ ግለሰቦች ሙስናን እንዲያጣሩ በጸረ-ሙስና ኮሙሽን የተላኩትን ሰራተኞችን ከዘረፉት ገንዘብ እንዲካፈሉ በማድረግ የተመሰረተባቸውን ክስ ማስረዝ በመቻላቸው በነጻ ተለቀዋል። የወንጀለኞችን ነጻ መውጣት ተከትሎ የአከባቢው ህዝብ ተቋውመውን በመግለጽ ላይ ነው፣
የህዝብን ገንዝብ በማባከን ወንጀል ተከሰው በእስር ቤት የቆዩ አቶ አብረሃለይ አበራ ፤ አቶ ሚካኤል ፤ አቶ ግርማይ ወሉና አቶ ዓለም ግዴና የተባሉ ግለሰቦች በተጨባጭ ማስረጃ ክስ ተመስርቶባቸው የነበሩ ተጠርጣሪዎች በሙስና የሚገለጽ ከባድ ወንጀል ፈጽመው ሲያበቁ ጉዳያቸው ተጣርቶ በህጋዊ መንገድ ውሳኔ መስጠት ሲገባ ህጋዊ ባልሆነ መንገድ እዲፈቱ መደረጉ የኢህአዴግን ስርዓት ሙስናን እውጋለሁ እያለ የሚደሰኩረው ከመርህ ሳይሆን ህዝብን ለማታለል መሆኑን የሚያመላክት ነው፣
በሌላ ዜና በአ/አበባ ከተማ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሰራተኞች የነበሩ ወ/ሮ ገነት ማስረሻና አቶ አባይነህ ጥላሁን የተባሉ ዜጎች የመንግስትን ሚስጥር አባክነዋልና የመንግስትን ንበረት ለግል ጥቅማቸው አውለዋል በሚል ሰበብ ሰኔ 25, 2005 ዓ/ም በወረዳ 14 በሚገኘው እስር ቤት መታሰራቸውን ከቦታው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣