Monday, July 8, 2013

ኗሪነታቸው በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሆኑ ነጋዴዎች ከአቅማቸው በላይ የሆነ ከፍተኛ ግብር እንዲከፈሉ እየተገደዱ መሆኑን ቷውቋል፣




በደረሰን ዘገባ መሰረት ኗሪነታቸው በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን፤ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ የሆኑ ብወርቅ ስራ ሞያና ንግድ የተሰማሩ ነጋዴዎች የኢህአዴግ ስርዓት በሚከተለው ብልሹ አሰራር ምክንያት ተጨባጭ የንግድ እንቅስቃሴንና የነጋዴውን ገቢና ወጪ በሚገባ ሳይጠና በኮታ መልክ ግብር እየተጣለ ነጋዴው ከአቅሙ በላይ የሆነ ከፍተኛ ግብር እንዲከፍል እየተገደደ ነው፣
በከተማዋ ከገቢያቸው ጋር የማይመጣጠን ከፍተኛ ግብር እንዲከፍሉ ከተፈረደባቸው ጥቂት ነጋዴዎች መካከል።-
1-አቶ በርሀ ነጋሽ የቀበሌ 04 ኗሪ ወርቅ ቤት ያላቸው 8 ሚልዮን ብር
2-መርጌታ ተኽላይ የቀበሌ 04 ኗሪ ወርቅ ቤት ያላቸው 11 ሚልዮን ብር
3-አቶ ታደሰ ወርቅ ቤት ያላቸው 11 ሚልዮን ብር
4-አቶ ልጃለም መኮነን ወርቅ ቤት ያላቸው ሁለት መቶ ሽህ ብር
5-አቶ ፍትዊ ወ/አረጋይ ወርቅ ቤት ያላቸው 120 ሽህ ብር
6-አቶ መዐሾ ትኩእ ወርቅ ቤት ያላቸው 120 ሽህ ብር
የሚገኙባቸው ሲሆን ነጋዴዎቹ በመንግስት እንዲከፍሉት የተወሰነባቸውን ከፍተኛ ግብር ዳግም እንዲታይላቸውና መሻሻል እንዲደረግላቸው ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ቢያቀርቡም ሰሚ  እንዳላገኙ ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላሉ፣