በደረሰን ዘገባ መሰረት የሰቆጣ ከተማ ኗሪዎች ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ንብረታቸውን ሳይቀር በመሽጥ
ያዋጡትን ገንዘብ የስርዓቱ ደጋፊዎች ለሆኑ ግለሰቦች በሽልማት መልክ በመሰጠቱ የከተማዋ ኗሪ ህዝብ የተዋጣው ገንዘብ ለምን ለፖለቲካ
ስራ እንዲውል ተደረገ በማለት በአንድ ድምጽ የተቋውሞ ሰልፍ አካሂዳል፣
የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ይመር ሰላማዊ ሰልፍ ለወጣው ህዝብ በሰጡት ምላሽ ስለተነሳው ጥያቄ
እስካሁን ድረስ የማውቀው ነገር የለም ወደፊት ጉዳዩን አጣርተን መልስ እንሰጣለን የሚል ሸፍጥ የተሞላበት ንግግር በማድረግ ሰላማዊ
ሰልፉ እንዲበተን ማድረጋቸውን ቷውቋል፣
በተመሳሳይ በሰኔ 26,2005 ዓ/ም በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን በጸለምቲ ወረዳ የሚገኙ መምህራን ቦንድ
ባለመግዛታቸው ምክንያት የሃምሌና ንሃሴን ደምዎዛቸው እንዲታገድ ተደርጓል፣ አስተማሪዎቹ መፍትሄ ፍለጋ ወደ ወረዳዋ አስተዳዳሪ በሄዱበት
ወቅት ሃላፊው ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በጽ/ቤታቸው እያሉ የሉም በማለት አስተማሪዎቹ እንዲባረሩ ማደረጋቸውን ከቦታው
የደረሰን ዘገባ ጨምሮ ያስረዳል፣