Friday, October 18, 2013

የሽረ እንዳስላሰ 2ኛ ደረጃ ተማሪዎች በመማር ማስስተማር ሂደት የሚታዩትን ችግሮች እንዲፈቱ በመጠየቅ አድማ አደረጉ፣




መስከረም 29,2006 ዓ/ም በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ በሚገኘው የፍረ ስውኣት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች የተደረገ አድማ ዋና መነሻ ት/ቤቱ ለመማርና ማስተማር የሚያስፈልጉትን ማተሪያሎችን ስላልተሟሉለት የተማሪው ውጤት ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ መጥቶ የ10ኛ ክፍል መልቀቅያ ፈተና ከወሰዱ አንድ ሽህ ተማሪዎች አንድ መቶ መቻ ነጥብ ማግኘታቸው ይህም አምባገነኑ ስርዓት ሆን ብሎ በአስተማሪነት ስም በት/ቤቱ የተመደቡት ካድሬዎችን በመጠቀም ተማሪዎችን በመጣል በውትድርና ሞያ ለመመልመል የሚደረግ ሴራ በመሆኑና የሚመለከተው አካልም መፍትሄ ሊሰጥ ባለመቻሉ መሆኑን ቷውቋል፣
ተማሪዎቹ ባደረጉት ተቋውሞ በያንዳንዱ የመማሪያ ክፍል በቂ ዴስክ እንዲኖር ፤ የመማሪያ መጻህፍት ለሁሉም ተማሪ እንዲዳረስ ፤ የፕላዝማ ትምህርት እንዲኖር ፤ብቃት ያላቸው አስተማሪዎች እንዲመደቡ ወዘተ የሚሉ ጥያቄዎች አቅርበዋል፣
ተማሪው አድማ ባደረገበት ጊዜ የተማሪው ቤተሰብ በት/ቤቱ የተገኙ ሲሆን ተማሪዎች ጥያቂያቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበዋል ጥያቂያቸው ትክክል መሆኑን ነገር ግን በበጀት እጥረት ምክንያት እንዳልተሟላ በማመልከት ለቀጣይ እንዲሟላ ይደረጋል የሚል ምላሽ እንደሰጡዋቸው ለማወቅ ተችሏል፣