በሰሜን እዝ በባድመ ግንባር የሚገኘው የ 23 ክ/ጦር አባላት ስርዓቱን በመክዳት ከነ ሙሉ ትጥቃቸው በመጥፋት
ላይ መሆናቸውና ፈቃድ አግኝተው ቤተሰብ ለመጠየቅ የሄዱትንም በዛው ስለሚቀሩ በክ/ጦሩ የሚገኙ አሃዱዎች የሰው ሃይላቸው እየተመናመነ
መጥቷል፣ በሁኔታው ተስፋ የቆረጡ የጋንታ አመራሮችም ፈቃድ ተሰጥታቸው ሳይመለሱ የቀሩት ወታደሮችን ይዘው እንዲያመጡ ተልከው በሄዱበት
እንደቀሩ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል፣
የስርዓቱ አምባገነናዊ ባህሪያትን ጨምሮ ከፍተኛ የሰራዊት መኮንኖች ቀደም ሲል ያቀረቡትን የደምዎዝ ጭማሪ
ጥያቄ ተቀባይነት ባለማግኘቱ በሰራዊቱ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ነግሶ እርስ በራሳቸው መግባባት ባለመቻላቸውና አብዛኛዎቹ ሞራላቸው
በመውደቁ አባሎቻቸውን መቆጣጠር ባለመቻላቸው የወታደሩን መክዳት አባብሶታል፣