Friday, October 18, 2013

በሸራሮ ከተማ መስተዳድር የቀረበ የ 2005 ዓ/ም የስራ አፈጻጸምና ለ 2006 ዓ/ም የተያዘው እቅድ የተመለከተ ሪፖርት በከተማዋ ኗሪ ተቀባይነት ሳያገኝ ቀረ፣




ጥቅምት 3,2006 ዓ/ም በተጠራው ህዝባዊ ስብሰባ የተገኙት የመስተዳድር አካላት የ 2005 ዓ/ም የስራ አፈጻጸም በዓመቱ በእቅድ ተይዞ ከነበረው ሁሉም በሚገባ መተግበሩንና ለ 2006 ዓ/ም የተዘጋጀው እቅድ ደግሞ ካለፈው ዓመት ከተገኙት አወንታዊ ተመክሮዎችን በመቀመር የተሻለ ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆኑን በመግለጽ የቀረበው ሪፖርት በስብሰባው በተገኙት የከተማዋ ኗሪዎች ተቀባይነት እንዳላገኘ ቷውቋል፣
ስብሰባው በወረዳዋ የአደረጃጀት ሃላፊ መምህር ተኽስተ የተመራ ሲሆን በስብሰባው የተገኙ የከተማዋ ኗሪዎች በ2005 ዓ/ም ህዝብን የሚጠቅም የተሰራ ስራ እንዳልነበረ በተለይም ልዩ ቱክረት ተሰጥቶት መፈታት የነበረበት
-ዓመታትን ያስቆጠረው የከተማዋ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር
-በት/ቤቶች የሚታይ የመማሪያ ክፍል ጥበትና የት/ት መርጃ መሳሪያዎች
-የቴለፎን አገልግሎት አለመኖር
-መልካም አተዳደር ያለመኖር በጉቦና ወገን መስራት
-ግብር ከአቅም በላይ ማለት ዝርፊያ ሊባል በሚችል ደረጃ እንድንከፍል መገደዳችን በዚህም ምክንያት በከተማዋ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መዘጋታቸውንና ሌሎች አስተዳደራዊ በደሎችን ጨምሮ በርካታ ያልተፈቱ ችግሮች እንዳሉ ገልጸው የቀረበው ሪፖርት እውነታን የሚያንጸባርቅ አይደለም በማለት ተቃውማቸውን ገጸዋል፣