Thursday, October 17, 2013

ለስኳር ፋብሪካ ግንባታ እየተባለ ከህዝብ ካዝና የሚወጣው በጀት በኢህአዴግ ባለስልጣናት እየተዘረፈ ነው፣




በሃገሪቱ የስኳር ፋብሪካ ፕሮጀችት እየተባለ በየዓመቱ የሚመደበው በጀት ለሚፈለገው ስራ ሳይውል በስርዓቱ ባለስልጣንት ይዘረፋል፣ በሚኒስትር ማእረግ የስኳር ኮርፖሬሽንን ሲመራ የነበረ አባይ ጸሃየ ከ 150 ሚልዮን ብር በላይ መዝረፉን ከደረሰን ዘገባ መረዳት ይቻላል፣
አባይ ጸሃየ በሰራው ወንጀል ተከሶ ወደ ፍርድ መቅረብ ሲገባው መ/ቤትን በመቀየር ወደ ሌላ የስራ መመደቡ ያልተዋጠላቸው የኮርፐሬሽኑ ሰራተኞች ዝውውሩን በመቋወም በስርዓቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ ገልጸዋል፣
በወልቃይት እየተገነባ ላለው ይስኳር ፋብሪካ ተብለው የሚላኩ የህንጻ መሳሪያዎች በተደጋጋሚ እንደሚዘረፉ መዘገባችን የሚታወስ ነው፣