Thursday, October 24, 2013

በአዊ ዞን የሚገኙ የአራት ወረዳዎች የመንግስት መ/ቤቶች በ 2005 ዓ/ም የበጀት ዓመት ከፍተኛ የገንዘብና የንብረት ብክነት ታየ፣




በአማራ ክልል ፤ በአዊ ዞን በእንጂባራ ፤ጃዊ ፤አንክሽና ትሊሊ ከነሃሴ 2005 ዓ/ም እስከ ጥቅምት 9,2006 ዓ/ም ባለው ጊዜ ከፌደራል ኦዲት ጽ/ቤት የተውጣጡ ባለሞያዎች ባካህሄዱት ምርመራ በ 2005 ዓ/ም የበጀት አጠቃቀም ውል አበል ከሚገባው በላይ ወጪ መሆኑን፤ ለወረዳ ግልጋሎት የተገዛ ንብረት ለግል ጥቅም መዋሉን ፤ የአላቂና ቋሚ እቃዎች ግዢ በሚፈጸምበት ጊዜ ከሻጮች ጋር በመመሳጠር አላግባብ የህዝብን ገንዘብ መዝረፍ የመሳሰሉ የሙስና ተግባራት ታይተዋል፣
የመስራቤቶችን እንቅስቃሴ በሚገባ እንዳይጣራ እንቅፋት ከሆኑት ባለስልጣናት መካከል
-አቶ ጌታቸው የወረዳ ት/ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ
-አቶ አስረስ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ሃላፊ
-አቶ ሞላ የንግድና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ሃላፊ
-ወ/ሮ ምትኬ የወረዳው ስቪል ሰርቪስ ሃላፊ
-አቶ ስሜነህ የኦዲት ጽ/ቤት ሃላፊ
ሲሆኑ በሙስናው እጅ ያላቸው በዞንና በክልል የሚገኙ የበላይ ሃላፊዎችን በመተማመን ሰነዶቹ ለምርመራ እንዳይቀርቡ ሲከላከሉ የነብሩና መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣