በደብረ ብርሃን ከተማና አከባቢዋ እየተስፋፋ የመጣውን የአንገት ገትር በሽታ ለመቆጣጠር የአከባቢው መስተዳድር
በሚፈለገው ደረጃ ሊንቀሳቀስ ባለመቻሉ ብዙ ዜጎች ህይወታቸውን እያጡ ነው፣ እስካሁን ድረስ ከ 50 በላይ የአከባቢው ኗሪዎች በበሽታው
ተጠቅተው ህይወታቸውን ማጣታቸውን ቷውቋል፣
በአከባቢው የሚገኙ የጤና ጣቢያዎች በበሽታው ተጠቅተው ወደ ህክምና የሚመጡትን በሽቶኞችን ተቀብሎ የህክምና
አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል በቂ መድሃኒትና የሰው ሃይል ዝግጅት ስለሌላቸውና ክፍተቱንም ለመሽፈን በሚመለከተው አካል እስካሁን
ድረስ የተወሰደ እርምጃ ባለመኖሩ በበሽታው የሚሞተው ሰው ቁጥር ሊጨምር ይችላል ሲሉ በጤና ጣቢያዎቹ የሚሰሩ ባለሞያዎች ይናገራሉ፣