Tuesday, October 15, 2013

በመቐለ ከተማ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን በመደገፍ ህዝብን ቀስቅሳችሃል በሚል በጽጥታ ሃይሎች የተያዙ ወጣቶች ያሉበት አድራሻ እስካሁን ድረስ አልታወቀም፣




ወጣቶቹ የፈጸሙት ምንም ዓይነት ወንጀል ባይኖርም ዓረና ትግራይንና አንድነት ፓርቲን በመደገፋቸው የከተማዋን ኗሪ ቀስቅሳችሃል በሚል መስከረማ 27,2006 ዓ/ም በስርዓቱ የጸጥታ ሃይሎች ታፍነው የተወሰዱ ዜጎች እስካሁን ድረስ ያሉበት አድራሻ በትክክል ካለመታወቁም በላይ የቀረበባቸው ክስ የለም፣ ከታፈኑት ዜጎች መካከል መምህር ስዓረ ፤ ኢንጂነር ነጋሲ ገብሩ፤ አቶ አንገሶም ተስፋይና ወ/ሮ ቅዱሳን ኣብርሃ (ነባር ታጋይ) ይገኙበታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በሽረ-እንዳስላሰ ከተማ ቀበሌ 03 ከጀርመን የህክምና ማእከል አከባቢ ዓረና ትግራይ አዲስ መስከረም 24,2006 ዓ/ም ጽ/ቤት የከፈተ ሲሆን በስነስርዓቱ በርካታ የከተማዋ ኗሪ ህዝብ ተገኝቶ እንካን ደህና መጣችሁ በማለት በጽ/ቤት በከፍተኛ ክብር የባንዴራ ማውጣት ስነስርዓት ተሳትፋል፣
በመክፈቻው ስነስርዓት አምባገነኑ የኢህአዴግ መንግስት ይውረድ! ፤ ሙስና ይወገድ!  ህጋዊና ዴሞካሲያዊ ስርዓት ይመስረት! የሚሉ ወቅታዊ መፈክሮች በጽ/ቤት በግልጽ ይታዩ ነበር፣