በሸራሮ ከተማ በሚገኘው የቻይና ካምፓኒ በጥበቃ ስራ ተቀጥረው ሲሰሩ የነበሩ የስርዓቱ ተላላኪዎች በውክልና
እንዲጠብቁት የተረከብቱን ንብረት ከነጋዴ ጋር በመመሳጠር በሌሊት አውጥተው ሸጠው ሲያበቁ እራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን በአከባቢው
በሚኖሩ የህብረተሰብ አባላት እንደተዘረፈ አስመስለው በማቅረብ 11 ዜጎችን በፖሊስ ተይዘው በእስር ቤት ውስጥ ታጉረው ይገኛሉ፣
ምንም ወንጀል ሳይኖራቸው ከታሰሩት የአከባቢው ኗሪዎች መካከል አቶ ሰጉም ተስፋይና አቶ ሙሉጌታ ግርማይ
የተባሉ ዜጎች የሚገኙባቸው ሲሆን በልዩ ቦታ ታስረው ቤተሰቦቻቸውን ጭምር እንዳይጠይቃቸው ታግደዋል፣ ካድሬዎቹ ከፖሊስ ጋር በመተባበር
እስረኞችን ወይ ሌባ ሁኑ ወይ ሌባ አምጡ በማለት እያሰቃያቸው መሆኑን የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፣
ይህ በእንዲህ እያለ በሸራሮ ከተማ መንግስት በነጋዴዎች ላይ የሚጥለውን ከፍተኛ ግብር አጠናክሮ በመቀጠሉ
በርካታ በከተማዋ የሚኖሩ ነጋዴዎች የንግድ ድርጅታቸውን በመዝጋት ላይ ናቸው፣ አቶ ቴዎድሮስ ኪ/ማሪያም ካፊቴሪኣያ የነበራቸው፤
አቶ አታኽልቲ ቤዚ የኮምፕዩተር ማእከል የነበራቸው 58 ሽህ ብር
ግብር እንዲከፍሉ የተጠየቁ ፤ ወ/ሮ ምሕረት ገብረአነንያ የኮምፕዩተር ማእከል ያላቸው 36 ሽህ ብር ግብር እንዲከፍሉ የተጠቁ ፤
አቶ ማእረግ አብረሃ የብረታ ብረት መሸጫ ድርጅት የነበራቸው እንደዚሁም አቶ ገብረሊባኖስ ሃደራ በከአማዋ ጋራጅ የነበራቸው የንግድ
ድርጅታቸውን ከዘጉ ነጋዴዎች ጥቂቶቹ ናቸው፣