Thursday, October 24, 2013

በባህርዳር ከተማ ለሚገኙ የመንግስት መ/ቤቶች የስራ ማስኬጃ እየተባለ የሚበጀት በጀት በሚፈለገው ስራ ላይ ሳይውል በመስሪያ ቤቱ ሃላፊዎች ይባክናል፣




የባህርዳር ከተማ የካብኔ አባላት ጥቅምት 7,2006 ዓ/ም ባደረጉት ስብሰባ ሙስናን የተመለከተ አጀንዳ ተነስቶ ተሰብሳቢዎቹ ሊግባቡ ባለመቻላቸው ስብሰባውን የሚመራ አካል ከፌደራል መምጣት አለበት በማለት ተሰብሳቢዎቹ ጥያቄ አቅርበዋል ፣ በቀረበው ጥያቄው መሰረትም አቶ አሰፋ ከሲቶ የተባሉ ከፌደራል የተላኩ ባለስልጣን ስብሰባውን እንዲመሩት ተደርጓል፣ በተደረገው ማጣራት በውሃና ማእድን ፤ በጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ፤ በመሬት ምዝገባና ኮንስትራክሽን ፤ በማዘጋጃ ቤትና በፍትህ ቢሮ የሚገኙ ሃላፊዎች በድምር ከ 600 ሚልዮን ብር በላይ መዝረፋቸውን በስብሰባው መጋለጡን ቷውቋል፣
በመጨረሻም ተሰብሳቢዎቹ በተጨባጭ በሙስና ተዘፍቀው የተገኙ ሃላፊዎችን ነጻ ተለቀው በሌላ መ/ቤት ተዛውረው እንዲሰሩ ሲደረግ አንዳንዶቹን ደግሞ በስመ ሙስና አሳበው በፖለቲካዊ እምነታቸው ከኢህአዴግን አይደግፉም በሚል ብቻ ጥፋት ሳይኖራቸው በጥርጣሬ እስርቤት ውስጥ ገብተው እንዲሰቃዩ እየተደረገ ነው በማለት በስርዓቱ ላይ ይላቸውን ተቃውሞ ገልጸዋል፣