በዞኑ መስተዳድር የተመራውና በፍኖተ ሰላም ከተማ በዳሞት ሆቴል በሚገኘው አዳራሽ ጥቅምት 8,2006 ዓ/ም
በተደረገው ስብሰባ በተቃዋሚዎች የሚደረግ ማንኛውንም እንቅስቃሴ በመከታተል ለሚመለከተው አካል የጠቆመ ማንኛውንም ግለሰብ በከተማ
ውስጥ ለቤት ማሰሪያ የሚሆን ቦታ በሽልማት መልክ ይሰጠዋል ሲሉ የዞኑ መስተዳድር የተናገሩ ሲሆን በተሰብሳቢው ህዝብ ግን የተሰጠ
ምላሽ አልነበረም፣
ይህ በእንዲህ እያለ በአዊ ዞን ፤ በጃዊ ወረዳ የሚገኙ ሰራተኞች በህብር ስኳር ፋብሪካና በጣና በለስ ፕሮጀክት
በጽ/ቤቶች ሃላፊዎች እየተገደዱ ለበርካታ ቀናት በጉልበታቸው የሰጡትን አገልግሎት ታስቦ የድካማቸው ውጋ እንዲሰጣቸው በመጠየቅ ላይ
ናቸው፣